Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback Saints Era - Volume 1 [Amharic] [Large Print] Book

ISBN: 1087922372

ISBN13: 9781087922379

Saints Era - Volume 1 [Amharic] [Large Print]

የቅዱሳን ዘመን ስንል ምን ማለታችን ነው?

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶር ሞት ተዋጅተን በትንሣኤው ዳግም የተወለድን ሁላችን፣ አምነን የዳንን አማኞች ብቻ ሳንሆን ቅዱሳን ለመሆን ተጠርተናል (ሮሜ 1፡7 ፥ 1ቆሮ 1፡2)። ቅዱሳን ማለት ለጌታ ለራሱ የተለዩ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ማለት ነው (ቲቶ 2፡14)። ቅዱሳንነት ጥሪ እንጂ ስም አይደለም። ይህም ጥሪ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ሳይሆን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ላመኑ ሁሉ የተሰጠ ጥሪ ነው። ቅዱሳን ለመሆን እንደተጠራን የነገረን የእግዚአብሔር ቃል፣ መጠራት ብቻ ሳይሆን በተጠራንበትም መጠራት መመላለስ እንዳለብንም ያሳስበናል (ኤፌ 4፡1)። ስለዚህም ነው ቅዱሳን የሚለው ቃል መጠሪያ ብቻ ያልሆነው።

ስለዚህ የቅዱሳን ዘመን ብለን ስንናገር፣ በቅድሚያ፣ ያመንን ሁሉ፣ ቅዱሳን (የተለዩ) ለመሆን ሁላችን እንደተጠራን እውቀቱ እንዲኖረንና በተጨማሪም በተጠራንበት መጠራት መመላለስ ደግሞ ሁላችን እንደሚጠበቅብን ግንዛቤ ውስጥ እንድናስገባም ነው። እነዚህን ሁለት ነገሮች መረዳትና በእነዚህ መረዳቶችም መመላለስ የቅዱሳንን ዘመን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱሳን ዘመን መምጣት አብሳሪዎች እንድንሆንም ያነቃቃል።

ይህ የመጀመርያ ቅጽ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፣ የመጀመርያው ክፍል የእግዚአብሔርን ቅዱስነት በተመለከተ የሚናገር ነው። ስለ ቅዱሳን ከመናገራችን በፊት የእግዚአብሔርን ቅዱስነት ማየትና መመልከት አስፈላጊ ነው። በሁለተኛው ክፍል ስለ ቅዱሳን ወይም ስለ ቅዱስ ሕዝብ እንመለከታለን። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር ነው ቅዱስ ሕዝብ ሊኖረው የሚችለው። እንዲሁም በመጨረሻው ክፍል ላይ በተለያየ ዘመን እግዚአብሔር የተለያየ የሥራ ትኩረት ሊኖረው ስለሚችል አሁን ያለው የሥራ ትኩረት ለማየት ዘመኑን ስለማወቅ እንመለከታለን። ዘመኑን ካላወቅን አሁን ያለንበትን ዘመን የቅǤ

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$25.32
Ships within 2-3 days
Save to List

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured