Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ [Amharic] Book

ISBN: B0G11QCRV5

ISBN13: 9798349622571

የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ [Amharic]

መንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ነው፤ ከአንድ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለት የራእይ ደረጃ ወደ ሌላ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለትና የራእይ ደረጃ የሚደረግ ጉዞ። ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ ቀጥተኛ ምሳሌ እንዲሆነን እግዚአብሔር ዘጸአት የተባለ የዕብራውያንን የጉዞ ዘገባ የያዘ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲቀመጥልን አድርጓል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ ከሌለን፣ ሕይወታችን ወደ ሃይማኖታዊነት ያሽቆለቁላል። ሕያው የሆነ የክርስትና ሕይወት ይዘት እንዳለን የሚታወቀው በምናደርገው የወደፊት ተራማጅ ግስጋሴ ነው። ጉዞ ካለ እንቅስቃሴ፣ እርምጃ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖ፣ ግብ ይኖራል። እነዚህ እሴቶች (values) ለሕይወታችን እጀግ አስፈላጊ ቅመሞች ናቸው። ይህ መጽሐፍ የክርስትና ሕይወታችን እንቅስቃሴ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖና ግብ እንዲኖረው ለማገዝ የተጻፈ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሕይወት በሌላ ቋንቋ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ተብሎ ይታወቃል። የዚህ መጽሐፍ ጽንሰ ሐሳብ የደረጀው በዚህ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ጅማሬ፣ ሂደት፣ ተግዳሮትና ግብ ላይ ነው።በዚህ መጽሐፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ወላጆችና ደቀመዛሙርት ሕይወት ቀረብ ብለን እንመለከታለን። የእነዚህ ደቀመዛሙርት ሕይወት የደቀመዛሙርትነት ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚያሳየን ብሉ ፕሪንት ነው። ይህንን ብሉ ፕሪንት አገላብጠንና ጠለቅ ብለን ከራሳችን ሕይወት ጋር በማዛመድ ለመመልከት እንሞክራለን። የደቀመዛሙርቱን ሕይወት ስንመለከት በመከተል ውስጥ ያሉትን አንዳንድ አንኳር ነገሮች መገንዘብ ብቻ ሳይሆን፣ የደቀመዛሙርቱን መምህር የበለጠ እያወቅነው እንመጣለን።

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$12.84
Ships within 2-3 days
Save to List

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured