Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback የሞተ ሰው ሀዘን: Yemote Sewu Hazen [Afrikaans] Book

ISBN: 1969702249

ISBN13: 9781969702242

የሞተ ሰው ሀዘን: Yemote Sewu Hazen [Afrikaans]

ከመጽሃፉ የተዎሰደ " ከመኪናው ሲወርድ ተበሳጭቶ ነበር። ለደቂቃዎችም
በዚኹ ስሜቱ ተጉዟል። ድንገት ሲዞር ያለፈበትን ያስተዋለ
ህሊናው ግን ብስጭቱን አሽቀንጥሮ ፍርሀትን አስተናገደ።
'ከትውልዱ ማን አስተዋለ?' ሲል የተገረመው ነብይ
ከየትኛው የዓለም እውነት ወደ'የትኛው የዓለም ብዥታ ዞሮ
ይሆን?
ወይስ ከብስጭት ወደ ፍርሀት ማደግ የዘመናት
ትውፊታችን ነው?
"ከተራ ብስጭት ቀጥሎ ባለ መፍራት ለማስተዋል
መገደዴ ምን ይፈይዳል" ሲል ዳግም የተበሳጨው በግማሽ
ልቡ ነበር። የፈራ ግማሽ ልቡ አካባቢውን መረመረ። " .............................................................

*****
እዚህ የተገኘበት የእራሱ አላማ ነበረውና በጥያቄ
ግዜ ማባከን አልፈለገም።
የውጭ ሀሳብ ማለት፣ መጠየቅ የምላሹ ግማሽ ሂደት
ሳለ ለጥያቄው ግዜ ባጣንለት ወቅት የሆነው ኹሉ ይሆን?
ግዜ ሳያባክን ቤተ-መቅደሱን ወዳቀፈው ጫካ ገሰገሰ።
ጫካው ጨለማውን ይበልጥ ያገዘፈ ነበር። የምናቡ
ሀሳቦችም መኖርን ባኮረፉ ግዜ የሆነው እንዲኹ መስሎ
ታሰበውና ሊስቅ ከማሰቡ ድንገት የሆነ ኮሽታ በድንጋጤ
ልቡን ለሁለት ሰነጠቀው።

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$27.57
Save $0.42!
List Price $27.99
Ships within 2-3 days
Save to List

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured