Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback የአዳም ቁጥር Ye'adam Kuter [Afrikaans] Book

ISBN: B0H73PC4GY

ISBN13: 9798184871646

የአዳም ቁጥር Ye'adam Kuter [Afrikaans]

እንዴት የሰው ልጅ በዚ ልክ ይህ ሁሉ ስሜት ይሰማዋል? ቢሉ ሰው የማይሰማው ስሜት የለም፥ ለዛውም ሴት ልጅ ፥ ለዛውም መኖር፣ ማጥፋት፣ መታረም፣ መቀጣት ማትፈራ እንዴት አይሰማትም?

በዝምታ መኖር ውስጥ ልብን ጭንቅ የሚያደርጉ፣ አይንን እንባ ሚጋብዙ፣ ብንፅፋቸው፣ ብናወራቸው፣ ብንጋራቸው ስሜታችንን የማይገልፀው ህመም እና ፍቅር ኡፍፍፍፍ.... ብለን መተንፈስ እንሻለን ፥ ቃል ቢያሳንሰው የእኔ ስሜት የአንዳንዶች ነበር በሚል እንደምንጋራ ታውቁ ዘንድ ይሄንን ግጥም ጀባ ብያለው።

ቁስሌን ለማን ላካፍል? ወዳጅ አልባ ብሶተኛ መሆን ተደማምሮ ያስወራል፣ ያፅፋል፣ ያስነብባል ።

የተጻፈን ለመኖር ከባድ ነው የተኖርነውን መጻፍ ግን ቀላል ነው። እየኖሩ መጻፍ ደስ ይላል! እየኖሩ ማውራት ደስ ይላል! እየኖሩ መምከር ደስ ይላል! እየኖሩ መሳቅ እየኖሩ ማልቀስ!

"እቺም ህይወት ሆና መከራ በዛባት" እንዳሉ እቺም እድሜ ሆና ስንቱን ኖርኩባት! ብዬ ሞነጫጨርኩ ለማ? ለእናንተ ለምን? እንድትረዱኝ አይመስለኝም ፥ ገጥሟቹ እንደው እንድትፅናኑበት በሚል፣ አልቅሳቹበት እንደው ከጎናቹ ሆኜ እየነፈረኩ ያለውትን እኔን ታስቡ እንደው ብዬ፣ አፍቅራቹ እንደው ተናገሩ፣ ኑሩ፣ ተሰበሩ ብዬ ፣ ጥፍጥና ከጎደለው ኖራቹ አጣፍጡት ብዬ፣ ሁላችንም የአዳም ቁጥር ነን ብዬ፣ አንድ ነን ስሜቶቻችን የጋራ ናቸው ብዬ፣ የጎደሉንን እየኖርን ነው ስህተታችንን እየተማርን ነው ብዬ፣ እንደ ትልቅ ሰው እንደ ልጅም ያልሆነ ያልረቀቀ ያልወደቀ የልብ የሆነ ቃል ለሰሚም ለአንባቢም አይከብድምና እንደ ገጣሚ ሳይሆን ህመም ፍቅር የምትጋራ ሴት አድርጋቹ ውሰዱልኝ።

አፌን ቃል ቢያጥረኝ ሆዴን ሆድ ቢብሰው
አይኔን እንባ ሞልቶ ልቤን ልብ አነሰው

እየኖርን!!!
___________________________________

ምሕረት መስፍን
2017 ዓ.ም

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$20.00
Ships within 2-3 days
Save to List

Related Subjects

Poetry

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured