የፕሬዝዳንቱ አዳኞችና አሳዳጆች
በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ነገር ይዞ የመጣው መጽሐፍ፤ ምንስ አዲስ ነገር አለው? ፕሬዝዳንቱ በታላቁ ስብሰባ ላይ በደስታና በፈገግታ ተሞልተው ንግግራቸውን እያደረጉ ነው። ነገር ግን በዙሪያቸው ስላለው አስከፊ አደጋ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጠንካራ ጠባቂዎቻቸውንም ሆነ ራሳቸውን ፕሬዝዳንቱን ለማጥፋት ስራውን የጨረሰ አደገኛ ኃይል አፍንጫቸው ስር ደርሷል። የተራቀቀ የስለላ መሣሪያ የሚጠቀሙ የደህንነት ተቋማት እንኳን ያልደረሱበት ጥልቅ ሴራ ዙሪያቸውን እየከበባቸው ነው... ስጦታ ለመስጠት ሳይሆን፣ ዓለምን ሊያናውጥ የሚችል አውዳሚ አደጋን ለማድረስ ያቺ የፕሬዝዳንቱ የመጨረሻ ፈገግታ ትሆን ይሆን?