ያለው እውነታ
ይህ ዕውነተኛ የሆነን ታሪክ ለማሳተም ታሪኩ በተጻፈበት ወቅትም ሆነ እከዛም በኋላ በትረስልጣኑን ተፈራርቀው በጉልበት አንቀው ይዘው የነበሩት አመጸኞች ታሪኩ የማይመጥናቸው መሆኑን ስላወቁ እንዳይታተም በቁርጠኝነት ተውረገረጉ ቢሆንም እነዚሁ መልከጥፉ ደም አፍሳሾችን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደየዕምነቱ ፈጣሪውን በፆም በፀሎት ተማፅኖ ተቆናጠው ከተኮፈሱበት ወንበር ተገፍትረው እስኪወረወሩ ሕትመቱ መጠበቅ ስለነበረበት ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ይኸው ለዛሬ አብቅቶን በፈጣሪ እርዳታ ለህትመት በቃ ተመስገን። ...በአኢትዮጰያ ሕዝብ ላይ መልኩን እየለወጠ ዘመን ለዘመን ተሸጋግሮ የሚመጣበትን ዕዳ ፍዳ መከራና ግፍ አልፎ ዛሬን ይሻላል ስንል የባሰው መጥቶ አቆረቆዘን።