Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback God is my Shepherd [Amharic] Book

ISBN: 1087865042

ISBN13: 9781087865041

God is my Shepherd

የእግዚአብሔር ስም አስደናቂ ስም ነው። "ስምህ ይቀደስ የሚለው" ጸሎት አንዱ የጸሎት ትርጉም ስሙን ከማስተዋል እንደሚመነጭ የሚነግረን ነው። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠራባቸው ስሞች አሉ። እነዚህ ስሞች የራሳቸው ትርጉም ያላቸውና እግዚአብሔርን በመረዳት በኩል የሚሰጡን ልዩ ትርጉም አለ። ስሙን ማስተዋላችን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት የተሳመጠ (intimate) ያደርገዋል። በዚህ መሳመጥ ውስጥ እግዚአብሔርን መለማመድ አለ።

በኒውማ ጽሑፍ የእግዚአብሔርን ስሞች በተመለከተ የቀረቡ ተከታታይ ጽሑፎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ያህዌ ይርኤ፣ ያህዌ ሻሎም፣ ያህዌ ንሲ የሚሉት ይገኙበታል። እነዚህ ሦስት የስሙ ትርጉሞችና ልምምዶች ከዚህ በፊት በወጣው "ያህዌ ንሲ- በዓላማ መኖር" በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ታትመው ለአንባቢ ቀርበዋል። አሁን ደግሞ "ያህዌ ሮኢ - እግዚአብሔር እረኛዬ" በሚለው በዚህ መጽሐፍ የእግዚአብሔርን እረኝነት በተመለከተ የጋራና የግል ልምምዶቻችንን የሚያጎለብቱ ጽሑፎች ቀርበዋል።

እግዚአብሔር "እኔ . . . ነኝ" መሆኑን በኢየሱስ ነው ያሳየው። እርሱ በኢየሱስ ሰው የሚያስፈልገውን ሁሉ ሆኖ መጣ። አሁን ትኩረታችንን የሚስበውና በመተንተን የምንመለከተው "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" የሚለውን ይሆናል። "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" የሚለው በዕብራይስጥ "ያህዌ ሮኢ" ይባላል።

የእግዚአብሔር እረኝነት የተገለጠው በጌታ ኢየሱስ ነው። እኛ እንደ በጎች እርሱ ደግሞ እንደ መልካም እረኛ ነው። የእርሱን እረኝነት በኑሮአችን ልንለማመደው ይገባል።

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$10.14
50 Available
Ships within 2-3 days

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2025 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured