Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback ጥሎ ማለፍ: Historical Novel [Amharic] Book

ISBN: 9994437569

ISBN13: 9789994437566

ጥሎ ማለፍ: Historical Novel [Amharic]

ይህ የሥነ-ጽሁፍ ሥራ በታሪካዊ ልቦለድነቱ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ወግም አስፈላጊው ትኩረት እንዳይነፈገው ጥረት ተደርጓል፡፡ የተወሰነ ዘመንን ተንተርሷል፤ ከደርግ አሥራ ሰባት ያገዛዝ ዘመን... አሥራ አራቱን፡፡ የዘመነ ደርግን ምሥጢራዊ ሰነዶችና መዛግብቶችን፤ ከተነሳበት ጭብጥ አኳያ ፈትሿል፡፡ በዚህም ጠቃሚ መረጃዎችን ለታሪካዊነቱ ዋቢ አድርጓል፡፡ "ታሪካዊ ልቦለድ በኃላፊ ጊዜ ቢጋር ውስጥ ተቀንብቦ ከባለታሪኮቹና ከመረጃዎች ጋር ቁርኝት ቢኖረውም፤ የዘመኑን ትንሣኤና ውድቀት አበክሮ ከማውሳት አያልፍም'' የሚለውን የብዕሩን ሰው የአንቶኒ ትሮሎኘን ነቢብ መደላድሉ አድርጓል፡፡ ከእንግሊዛዊው የታሪካዊ ልቦለድ ደራሲና ገጣሚ ከሮበርት ግሬቭ የግል አስተያየት ጋርም ደራሲው የሚስማማበት ነጥብ አለው፡፡ ግሬቭ፤ "እራሴን ወደ ቀድሞ ዘመንና ትዝታዎች የመመለስ ስጦታው አለኝ፡፡ በዚህም ትናንት ምንና እንዴት እንደነበር ማየት እችላለሁ፡፡ ታሪካዊ ልቦለድም መጻፍ ያለበት በዚህ መልክ ነው፡፡'' ይላል፡፡ ይህ ታሪካዊ ልቦለድ ባንድ የደርግ ቋሚ ኮሚቴ አባል በነበረ ግለሰብ ሕይወት ዙሪያ የተጠነጠነ ነው፡፡ የግለሰቡን መነሻና መድረሻ፣ ከደርግ ሥልጣነ ዘመን ቆይታ ጋር ይመለከታል፡፡ በአብዮቱ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ያብዮተኞች እጣ ፈንታና መጨረሻ ምን እንደነበር በመረጃዎች ተደግፎ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ጥበብ አኳያ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ ሥልጣን ያሰከራቸው ለማንም ለምንም እንደማይመለሱ ተስተውሏል፡፡ አንድ ዕውቅ ያገራችን ባለቅኔም፤
'አንቺ የሥልጣን ፅዋ፣ ሲይዙሽ በተራገፈታሽ ጣፋጭ ነው፣ ጭላጭሽ መራራ፤ይኸንን እያየ፣ የሚተውሽ የለምይጋደልብሻል፤ የሰው ልጅ ዘላለም፤' ሲሉም የባለጊዜዎችንና የመንበራቸውን ፍጻሜ ያመለከቱት ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡


Recommended

Format: Paperback

Temporarily Unavailable

We receive fewer than 1 copy every 6 months.

Save to List

Related Subjects

Fiction Literature & Fiction

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured