Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback ሜሪቶክራሲ: ሜሪቶክራሲያዊ ማሕበረሰብ &#4877 [Afrikaans] Book

ISBN: B0HNP764CZ

ISBN13: 9798163818235

ሜሪቶክራሲ: ሜሪቶክራሲያዊ ማሕበረሰብ ግ [Afrikaans]

የአንድ ሀገር የሥልጣኔ ማማና የሉዓላዊነት ጽናት የሚለካው ተቋሞቿን በሚመሩት ልሂቃን የዕውቀት ጥራትና የአስተዳደር ብቃት ልክ ነው። ይህ መጽሐፍ "ሜሪቶክራሲ፡ ሜሪቶክራሲያዊ ማሕበረሰብ ግንባታና የርዕዮተ-ዓለም ጥያቄ በኢትዮጵያ" በሀገራችን የፖለቲካና የማሕበረሰብ ታሪክ ውስጥ ለዘመናት ችላ ተብሎ የቆየውን፣ ነገር ግን የሕልውናችን መሠረት የሆነውን የ"ብቃት ሥርዓት" (Meritocracy) ጥልቅ ምሁራዊ ፈተና ይዞ የቀረበ የሕሊናና የሳይንሳዊ ምርምር ውጤት ነው።

የዚህ መጽሐፍ መወለድ መነሻው በቻይና ቤጂንግ የሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ትምህርቴን በምከታተልበት ወቅት የታዋቂው አሳቢ የዳንኤል ቤልን "The China Model: Political Meritocracy and the Limits of Democracy" የተሰኘውን መጽሐፍ ለማንበብ ካገኘሁት ዕድል ይመነጫል። ቤል በአሜሪካ ድንገተኛ የምርጫ ፖለቲካ (Democracy) እና በቻይና የአስርት ዓመታት የደረጃ በደረጃ የብቃት ማጣሪያ (Meritocracy) መካከል ያደረገው ንጽጽር የራሴን ሀገር ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታ ወደኋላ መለስ ብዬ እንድመረምር ትልቅ የሕሊና ቀስቃሽ ሆኖኛል።

ለረጅም ዘመናት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰማይ ሥር የሥልጣንና የሀብት ምንጮች ዕውቀት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ሳይሆኑ የጦርነት ኃይል፣ የርዕዮተ-ዓለም አምባገነንነትና የብሔር ኮታ መዋቅሮች ሆነው ቆይተዋል። ይህም ሀገራችንን ለችሎታ ማነስ (Mediocracy) አዙሪትና ለምሁራን መሸማቀቅ ዳርጓታል።

መጽሐፉ ይህንን መዋቅራዊ ስብራት ለመጠገን ከኮንፊሺየስ ፍልስፍና እስከ ሲሊከን ቫሊ፣ ከብሪታንያ የኖርዝኮት-ትሪቬልያን ሪፎርም እስከ ሲንጋፖር ያሉትን ዓለም-አቀፍ ተሞክሮዎች በስፋት ይዳስሳል። በተለይም የጆን ሮልስን የፍትሐዊነት መነጽርና የነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝን የስልጣኔና የቢሮክራሲ ጥራት እሳቤዎች በማነጻጸር ጥልቅ ፍልስፍናዊ መሠረት ያቀርባል።

ከዚህም በተጨማሪ መጽሐፉ፣ በአሁኑ ወቅት በአገራችን እንደ መፍትሔ የተወሰደውን የ"መደመር ፍልስ

Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$19.99
Ships within 2-3 days
Save to List

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2026 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Notice | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured